የትምህርት ክፍል መረጣ

yatemeherete-kefele-marathaa

ጭብጡ ስለ ዲፓርትመንት ምርጫ ሁኔታ የሚያትት ሲሆን ፀሀፊው የራሱን እይታ ከህይወት ልምዱ ጋር አዳምሮ ከትቦታል። እንደምክርም ቢጤ የሚመስለው ይህ ፅሁፍ መነሻው ፀሀፊው ከአንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ ጋር በነበረው ቆይታ የራሱን ልምድ ለማስተላለፍ ነበርና ይህን ምክር ለብዙሃኑ ይደርስ ዘንድ እዚህ አቅርቦታል።

ስለዲፓርትመንት (የትምህርት ክፍል) መረጣ ላይ አንዳንድ ሀሳቦች ላንሳ

ዲፓርትመንት ስንመርጥ ሁለት ፅንፍ ያሉ ሀሳቦች ይኖራሉ ብዬ አስባለው። አንደኛው በፍላጎት የምንመርጠው እና ገበያው 'ሚፈልገው ምናልባት በፍላጎት የምንመርጠው ገቢያ ላይ ዋጋው እምብዛም የሆነ...በኛ ሀገር ላይ የማይሰራበት ፊልድ ብዙ ይኖራል። ፍላጎትን ማስተናገድ በጎ ሆኖ ሳለ አንድን ት/ት ስንማር End goal(የመጨረሻ ውጤቱ) ስራ መያዝ መሆኑ ሚያግባባን ይመስለኛል። ታዲያ ተመርቀን የስራ ማጣትን ሁኔታ ለስምንት ወር አይቼዋለው። በዚህ የስራ-ፈትነት ዘመን 4 ኪሎን ዞሬበታለው፣ የስራ ማስታወቂያ አይቼበታለው ሲያልፍም ስልኬን ተሰርቄበታለው...እንዲህም አልፌበት 4ኪሎ ለኔ የሆነ ስሜት አለውና "4ኪሎን ሽቅብ ሣማትር" ጭምር ብዬ ከትቤለታለው... ያው መልዕክቱ ለሌላ ቢሆንም የታሪኩን ፍሰት በ4ኪሎ ላይ አድርጌዋለው። በስራ ማጣት ውስጥ የጎረቤት ጥያቄ ስራ አገኘህ፣ አየሩ ጥሩ ነው እያሉ ሚያከታትሉብኝ ጥያቄ...ከጥያቄነቱ ይልቅ ሽሙጥ ወይም ሃሜት መስሎኝ ኖሮ 4ኪሎን 6 ኪሎ መዘዋወርን የሙጥኝ ያዝኩ። የተማርኩት ፊልድ አንደኛ ምርጫዬ አልነበረም። ፍላጎቴ የነበረው የንግድ ስራ ት/ት(Business dep't) ነበር። ያንንም ለማሳካት ካለሁበት dep't ዝውውር ጠይቄ ወደ የምፈልገው የት/ት ክፍል ብሄድም እንዳሰብኩት አላስተናገዱኝም። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች እንደኔው ካሉበት የት/ት ክፍል ወደሄድኩት የት/ክፍል ለመቀየር እይሞከሩ ነበርና።  በአጋጣሚ የፈለኩት ባይሳካም plan B ያቀድኩትን ት/ት ተማርኩት...ጨረስኩት..አነሰም በዛም እየሰራሁበት ነውና።

-Welcome fresh program ላይ የዩንቨርሲቲው department head ስለ ትምህርት ክፍላቸው የሚያደርጉትን ገለፃ መከታተል ጥሩ ነው። ያው ሁሉም ስለራሱ ጥሩ ጥሩውን መናገር ይፈልጋል። ስለነገሩ አንዳንድ ነገር ግልፅ ያደርጋል።

-በይነ-መረብ ላይ ስለምንመርጠው ት/ት መረጃዎችን መቃረም አስፈላጊ ነውና።

-በዲፓርትመንቱ ላይ የተመረቀ ሰው ካለ ወይም ከግቢ ውስጥ Senior ወይም GC ካለ እርሱን መጠየቅ።

       *በዲፓርትመንቱ ላይ የተመረቀው: ት/ቱ በስራ-ዓለም ላይ ያለውን አንድምታ ይጠቁመናል። የሰራ እድልም መኖር አለመኖሩን ይነግረናል።

      *ከግቢ ውስጥ Senior/GC: ስለት/ቱ ክብደት...interesting መሆኑን..ያለውን challenge ሊነግሩን ይችላሉ።

አንድ ሰው ምን አጫወተኝ የሆነ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ያሉ fresh ተማሪዎች ምን እንማር ብለው ሲያስቡ ምን ተጠቆሙ ዩንቨርሲቲው አካባቢ የሚሰራ ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ስለሚኖር...ይህ project ብዙ የስራ እድል ስለሚፈጥር ይህን ስራ ለመስራት የሚሆን አዲስ የሆነ Engineering field እንዲመርጡ ተደርገው ተመርቀው ሲወጡ ፋብሪካውም አልተገባምን፤ የተነገራቸው ያልተጨበጠ ቀቢፀ ተስፋ ሆኖ ለልጆቹ ቀረ፣ እነርሱንም አከሰረ።

መንግስት የት/ት ፖሊሲው ከ70 natural/30social የነበረው...ካለፉት 2 ዓመታት ወዲህ ወደ 55 natural 45 social ሆኗል። ይህም social የፋይናንሱን፣ የመዋዕለ-ንዋዩን ዘርፍ የሚያንቀሳቅስ ሆኗል። ለዚህም ነበር ከቻልሽ extension ሌላ social course ብትወስድ/ጂ ጥሩ ነው ያልኩት። አይታወቅም ምን ይዞልን እንደሚመጣ ሁሌም ራሳችንን ስናበቃ ፈላጊዎቻንን በፊታችን ይርመሰመሳሉ።

በአጠቃላይ ፍላጎት መርና ገበያ መር ዲ/ት ምን እንደሆነ እንለይ...ፍላጎታችንን እያስተናገድን... ለእንጀራ ሚሆነንን ለጎን እንማር።

ካለፈው የቀጠለ°°°

ከዚህ ቀደም ላነሳናቸው ሀሳቦች ሁሉ መሰረት ሊሆን የሚችለው ነገር እቅድ(planning) ነው።

በፈለግከ/ሽው የጊዜ ርቀት አቅጂ...የታቀደውን ለማሳካት ጥረት ይፈልጋል። ኋላም የሚመጣው ውጤት በጎም ይሁን መጥፎ የመቀበልና የተበላሸውን እንደገና የማስተካከል ስነ-ልቦና ማዳበር ያስፈልጋል።

- ራስ ላይ መስራት:- ራስን መገንባት አስፈላጊ በስነ-ልቦና፣ በእውቀት፣ በአካል ጥንካሬ ማለት ነው። የአእምሮ ና የአስተሳሰብን ልህቀት(Intelligence) 'ሚያጎለብተው አንዱ መፅሀፍት ማንበብ ነው። መፅሀፍት ከእውቀት ምንጭነት በዘለለ አስተሳሰብን ማዳበር፣ ንግግር ብስለት የማምጣት አቅም አለው። ራስሽን ለልቦለድ፣ በታሪክ፣ ሀይማኖት፣ አስተዳደር....የተተየቡትን መፅሀፍት አንብብ/ቢ...ላንተ/ቺ አንዱ ትልቅ ግብዓት ይሆናል። plan ስታደርግ/ጊ በወር ውስጥ ይሄን ያህል መፅሀፍ አነባለው ብለሽ አቅድ/ጂ።

- ራስን በስልጠና ማዳበር:- አሁን በቴሌግራም ላይ ከሚለቀቁት ስልጠናዎች በዘለለ...ሌሎች ለወደፊት ለስራ-ህይወትህ/ሽ የሚጠቅሙህ/ሽን እድሎች መጠቀም ያስፈልጋል። ለምሳሌ:- ድሮ በEnglish period ስለ letter አፃፃፍ ስንማር ብዙም ትኩረት ያልሰጠሁት ነገር ስራ ላይ formal ደብዳቤ አስፈላጊ እንደሆነ አይቻለው። Report writing skill አስፈላጊ ነው....ለዚህ ደግሞ AAU ሌላውም የትምህርት ተቋም በብዙ ዘርፎች training ይሰጣል...ስለReport writing(የቢሮ ደብዳቤ) እንደሚሰጥ አውቃለው እና Office Memo አፃፃፍ ደግሞ google ላይ check ማድረግ ትችያለህ/ሽ....በዛ ላይ chat- gpt አለ...ለማጨናነቅ ሳይሆን ክህሎቱን ማወቁ አይከፋም።

- LinkedIn account መክፈት ጥቅም አለው ነገር ግን አካውንት ላይ የምናስገባቸው ድርብርብ ማዕረጎች እኛን ማይወክሉን ከሆነ ራስን መሸወድ ይመስለኛል(B.analyst, Economist, digital marketers, game changer) እያልን ለራሳችን ምንሰጣቸው ነገሮች አሉ። በተቻለ መጠን "ሰው ፊት ራሳችንን ስናቀርብ ያለንን፣ ምንችለውና ምናውቀውን ብቻ እናሳይ። ሆነን ስንገኝ ይሄን ማዕረግ ብንደርበውም አይቆጭም።"

Comments (1)
No comments yet