ምትኬ ወዴት አለሽን?

metekee-wadeete-alashene

እንደ ድሮ ዘመን ድብ አንበሳ አስመትቼ፣ ንስር ቃና አስነፍቼ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሠራዊቴ ጋር በዱር በገደሉ አልፈልጋት… ለመኳንንቶቼ በገሃድ አዋጅ አስነግሬ… በጥሩንባ አስለፍፌ አላስመጣት ታዲያ ያለኝ አማራጭ በድንገት መ/ቤቱ ከመጣች የሚል ሆነ… ነገር ግን እሷን የበላው ጅብ አልጮህ አለ። ፈጣሪዬን አንድ ነገር እጠይቃለሁ።… በእውን እሷ የእኔ እጣፈንታ ከሆነች ከሆነች እባክህን አንድ እድል ስጠኝ እለዋለው… ካልሆነች ግን ከልቤ ላይ አጥፋት። አንቺም ይሄን ካየሽ ወደኔ ትመጪ ዘንድ ወደድኩ። አሁንም ምትኬ ወዴት አለሽን እያልኩ ከአድማስ ባሻገር ቆሜ እጣራለው!

ምትኬ ወዴት አለሽን?

አንድ ሀሳብ ወደ ውስጤ መመላለስ ከጀመረ ዓመት ሊያስቆጥር የወራት እድሜ ብቻ ነው የቀረው ብቻ አልሣካ ያለ… የሚመስል… አንድ ሰሞን ወደ የኔ የመጣ ዕድል መሣይ ግን እንዲሁ ሳልጠቀም እያየሁት በዋል ፈዛዛ ያለፈኝ… የሚገርመው የነገሩ ማለፍ ሣይሆን በጊዜ እርቀት እንኳን ትውስታው ሣይከስም በልቦናዬ ይንከላወሣል… ዛሬም ጭምር ይልሞሠሞሣል… ወጣትነት ፍም እሣት ነው… የምንፈልገውን የምናገኝበት የሚመስለን… ካገኘነው የምንወዳጅበት… ውበት የሚጎላበት… ስሜት የሚነድበት… ጉልበታችን የሚጠነክርበት… ከራስ በላይ ንፋስ የምንልበት ነው ይህ ወጣትነት… ታዲያ ይህ የእድሜ ዘመን ለተቃራኒ ፆታ የሚኖረን ስሜት የሚጎላበት… በፍቅር የምናብድበት ጊዜ ነው። መቼስ በዚህ የእድሜ ዘመን ላይ ሆኖ ይህ የማይሰማው አይኖርም። ስለፍቅር በየቦታው፣ በየማህበራዊ ሚዲያው፣ በየትራንስፖርቱ ሲያልፍም በየስራ ቦታም ሣይቀር እሠማለው… መቼስ በዚህ መሃል ራሴን መጠየቄ አይቀርም። አዎ አንተ ወዳጄ መች ይሆን የራስህን ሔዋን የምትፈልግ እላለው። አንዳንዱ የፍቅር ታሪኩን ሲያጫውተን ምን ያህል እንስት በፍቅር ምክያት ሲያመላልስ እንዳቆየ ሲነግረን ወደ ራሴ ገብቼ አሁንም አንተ ሆይ! ምን ትሠራለህ ሰው ይሄን ሁሉ ሲያመላልስ እለዋለው… ህሊናዬ ግን ይሄን ሃሣብ በምሉዕነት አይበቀለውም። ማለትም ጓደኛ እንዲኖረን እሱም በጥብቅ ቢያምንበትም አንድ ለአንድ የሆነ ወደ ትዳር የሚወስድ ጓደኝነትን እንጂ በአንፃሩ ከላይ እንደተባለው አንዷን በአንዷ እየተካ ስጋዊ ፍላጎትን ማርካት አይደለምና። ስለ ዕድሜዬም ሣነሳ አዎ ጥሩ ላይ ነኝ አንድ እዩቤልዩ ላይ ነኝ… አዎ ለማጨትማ ደርሻለው ችግሩ ግን ማንን ነው የሚለውን ነው?

ይህን ሣስብ አንድ አመት ወደ ኋላ የሚጠጋ ጊዜ በምናብ ራሴን አሣፈርኩ። አቧራ ከጠጡ ትውስታዎቼ አራግፌ ምን ነበር… ማን ነበር እያልኩ የትውስታ ማህደሬን ማውጠንጠን ጀመርኩ… ከትንሽ ተመስጥኦ በኋላ 2016 ክረምት ወራት ላይ ራሴን ቁጭ ብዬ አገኘሁት። ጊዜው ሃይለኛ ዶፍ የሚወርድበት፣ ዝናብ ጎርፉ ሠው የሚያሣድድበት፣ ብርዱ፣ ቅዝቃዜው ቆፈን የሚለቅበት፣ ጉሙ ሰውን የማያስተያይበት በቃ ተፈጥሮ አለሙ ከርሞውኑ በደመና ጢስ የሚታወድበት የሐምሌ የክረምት ወቅት… ካለፈው 2 ዓመታት ወዲህ በክረምት ሙሉ ቀን መተኛት የለም ት/ቤት ተዘግቶ ማረፍ የለም… አሁን ስራ ነው ወዳጄ ጎህ ሲቀድ ማለዳ ትነሳለህ ወደ ስራህም ትከንፋለህ… ማታ ጀንበር ስታዘቀዝቅ ወደ ቤትህ ታዘግማለህ። መ/ቤታችን ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የApparent/ internship ዕድል በክረምት ያመቻቻል። በስራ ቦታ እያልን አዲስ ፊት ስናስተውል ተማሪዎች እንደሆኑ እናስባለን።

ነገር ግን ሁሌ አይደለም ምከንያቱም አዲስ ቅጥርም ሊሆን ይችላልና። መቼስ አዲስ የአላፊ አግዳሚውን ፊት ስናማትር ስናይ በቃ ይችንማ ተፍተፍ በልባት ይሉኛል። እኔም በባዶ እንዳለው ለጊዜው ዘንግቼው ለሌላው ሠው መምከሬ አልቀረም። በዚህ መሃል የማስተውላት አንዲት ልጅ ነበረች እሷም በintern እንደገባች አውቃለው ብዙ ጊዜ ካፌ ውስጥ አያታለው… እንተያያለን። ነገሩን በቀላሉ ያየሁት እኔ… ጊዜ በቆጠረ ቁጥር ለልጅቷ ያለኝ ስሜት እየጨመረ መጣ። ከጓደኞቿ ጋር ካፌ ተጠቅማ ስትወጣ አይኔ እሷን እሷን እያማተረ በሃሣብ ይዋጣል። ይህንንም የስራ ባልደረቦቼ አይተውኝ ኖሮ መሣቂያ መሳለቂያ ካደረጉኝ ሠነባብተዋል። ተክለቁመናዋ ለኔ ሊስማማኝ የሚችል ነው… ጓደኛዬ ግን ይህችን 4በ4(አራት በአራት) የሆነች ልጅ ምን ልታደርጋት ነው ይለኛል። እኔም ውበት እንደተመልካቹ ነው እለዋለው(Beautiness is in the hands of the beholder.)

ቁመቷ አጠር ያለ(ማለቴ ለሴት አሪፍ የሚባል ነው።) ሠውነቷ ወፈር ያለች ደርባባ… ከወገቧ በታች ሠፋ ያለች “ኮካ ኮላ” ነገር ናት ብቻ የምትመች የምትመስል… ፀጉሯን ብዙ ጊዜ ሹሩባ ታዘወትራለች ምናልባትም የክረምቱን ወቅት ለመቋቋም ይሆናል… በረጅሙ ትሠራዋለች ራስታ ይመስላል የፀጉር ስታይሏ ብቻ ሲያምርባት ደግሞም ከጠይም መልኳ ጋር ተዳምሮ መልከ-መልካም ሀበሻዊት አስመስሏታል። ይህን ያህል ስለሷ ካልኩ ልጅቷ በapparent ወደ መ/ቤቱ ስትገባ ለመመረቅ አመት ግፋ ቢል 2 ዓመት እየቀራት ነው። የት/ቷን ዘርፏን ለማወቅ ከምትሠራው ሥራ ጋር ማዛመድ በቂ ነው። ሌላው ቢቀር እኛ ቢሮ ከአንድ 2,3 ጊዜ መጥታ አጠገቤም ብዙ ደቂቃዎችም ቆማለች… አይናፋርነት… የሚያጠቃት የምትመስለው ይህች እንስት ሳያት ልቤ ይከንፋል። ቢሯችን እሷን ጨምሮ ሌሎች የስራ ባልደረቦቿም መጥተው ነበርና ከአንድ senior ባለሙያ ጋር አንድ ስራ ተሠጥቷቸው እንዲሠሩ/ እንዲለማመዱ ይደረግ ነበርና።

የኮምፒውተር system ልናስተካክል ነው ብለው መጡ እኛም ይሁን ብለን ቦታችንን ለቀን ዳር ቆመን ማየት ጀመርን… “ሙያውን ለባለሙያው” እንደሚባለው በየቢሮው ያለውን system ያስተካክላሉ ተብለው የተላኩት ልጆች ጭራሽ ጤነኛ የነበረውን system አበላሹት ከዛ በኋላ ስንት ጊዜ IT ቢሮ ተመላልሰን በመጨረስም ተስተካከለልን። ሌላ ጊዜም የተበላሸ “printer” ቁጠሩ ተብሎ ልጅቷ ከአንድ ጓደኛዋ ጋር መጥተው የተበላሸ ዕቃ ሲቆጥሩ አስታውሳለው። ልጅቷን ከፎቅ ላይ ሆኜ ካየኋት ከአይኔ እስክትጠፋ ድረስ አያታለው። ታዲያ ይሄ እኮ ልክፍት ቢሉት ማጋነን አይሆንም። አንድ የስራ ባልደረባችን እነዚህ ተለማማጆች ቢሯችንን አዘውትረው ስለሚመጡ ከርሷ ይልቅ ሌላ ልጅ ጭምር ጠርቶኝ አስተዋውቆኛል። ተፍተፍ እንድልም ብዙ ቢወተውተኝም ሃሣቤ ወደዛ አልሄደም። ከምሠራው ስራ ስረዳ ልጅቷ computer ጋር የሚዛመድ ት/ት እንደምትማር ተረዳሁ… ለምሣሌ ወይ computer science, Inf. Technology, Info science, software engineering ሊሆን ይችላል።

ዕድሌን ላለመጠቀሜ ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም ከዛ ውስጥ የኔ ነገሮች ላይ አለመፍጠን፣ ማፈር፣ መፍራት አይነት ስሜቶች ስለተጠናወተኝ ወደዛ መድፈር አልቻልኩም… ሌላው ግን በዚሁ ሀምሌ ወራት መጀመሪያ ለምወዳት ኋላም ላልተሳካው ለመስኮቧ ለመጀመሪያ ጊዜ ፅሁፌን የሠደድኩላትም በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት ላይ ነበርኩና። ከእርሷም ተስፋ ሣይኖረኝ አይቀርም በሚል ይሆናል ለዛም ይመስላል መልስን ስጠብቅ ነገሮችም ሊያልፉኝ የቻሉት…

ከአንደኛው ፅሁፍ በኋላ ምላሿን በስልክ ተነግረን ብሠማም ተስፋ ሣልቆርጥ በዚህ አመትም ሌላኛውን ፅሁፌን ሠደድኩ ይሄኛው ግን እንደቀደመው ተስፈኛ ሣይሆን ተስፋ ቢስ የሆነ በእርሷ ተስፋ የቆረጠ እንደሆነ የሚገልፅ ዘለግ ያለ ፅሁፍ ነበር… ግን ነገሮች እንዳልሆኑ ሆነው… ጥቁር አሻራቻውን አሣርፈው አለፉ… እርሷም ልቤን የትም ትታው አለፈች… እንኳንም ትታኝ አለፈች የኔ አይደለችምና።

ወደ ቀደመው ሃሣብ ስነሳ በአይን ፍቅር ላይ የነበርኩት እኔ ወደ ዘላቂው ነገር ለመግባት ዳር ዳር የምለው እኔ… እንዲሁ እንዳለው… የት/ት final exam ደረሰብኝ 5 አካባቢ course ስለነበር ይህን ቢሮ ሆኜ ከስራ ጋር መጨረስ ስለማልችል እረፍት ሞልቼ ወጣሁ። ከመውጣቴ በፊት ግን ከፎቅ ላይ ሆኜ ልጅትን በድንገት ባያት ለማስታወሻ እንዲሆን ስልኬን አውጥቼ ከሩቅ ፎቶ አነሣኋት። በልቤም “ዛሬ ደግሞ ከልቧ አምሮባታል” አልኩ። ፎቶውን ከስልኬ ማህደር ሰንጄ ከሣምንት በላይ ከስራ ገበታዬ ተገልዬ ማንበብ ጀመርኩ… ታዲያ እረፍቴን ጨርሼ ስመለስ እርሷም በግቢው የለችም… ባፈላልግም አልተገኘችም… የማዋየው ባጣ ለስራ ባልደረባዬ አጫወትኩት እርሱም አይቷት እንደማያውቅ ነገረኝ። ከዛ ወዲህ ዘንድሮም ትዝታዋ ሲመጣብኝ ተኝቼም… በስራ ቦታው ስለ እርሷ ሳስብ እርሷ ከጎኔ እንደሆነች ይሠማኛል። እንደ ድሮ ዘመን ድብ አንበሳ አስመትቼ፣ ንስር ቃና አስነፍቼ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሠራዊቴ ጋር በዱር በገደሉ አልፈልጋት… ለመኳንንቶቼ በገሃድ አዋጅ አስነግሬ… በጥሩንባ አስለፍፌ አላስመጣት ታዲያ ያለኝ አማራጭ በድንገት መ/ቤቱ ከመጣች የሚል ሆነ… ነገር ግን እሷን የበላው ጅብ አልጮህ አለ። ፈጣሪዬን አንድ ነገር እጠይቃለሁ።… በእውን እሷ የእኔ እጣፈንታ ከሆነች ከሆነች እባክህን አንድ እድል ስጠኝ እለዋለው… ካልሆነች ግን ከልቤ ላይ አጥፋት። አንቺም ይሄን ካየሽ ወደኔ ትመጪ ዘንድ ወደድኩ። አሁንም ምትኬ ወዴት አለሽን እያልኩ ከአድማስ ባሻገር ቆሜ እጣራለው!

ውስጤ ስለምን አንቺን አንቺን ይለኛል… ስሜቴ ስለምን ይናወጣል… በመዓልትም፣ በሌሊትም የማይታወቅ ውዥንብር ስለምንስ ሆነብኝ የማትሆኝኝ ከሆነስ ውቃቤሽ ከላዬ ለምን አልራቀም። ተግደዳሪ ፆም አዳሪ እንደእባለው… የተፈለገውን ነገር በዛ ጊዜ ውስጥ መጠቀም ያልቻለ ዕድል በራሱ ይጫወትብሃል። መሸነፍን አምኖ ካልተቀበለና ሌላ በጊዜ ለመጠቀም እስካላሠበ ድረስ። “ለኔ ካለ ፈጣሪዬ ሆይ ምራኝ… በቀናው ጎዳና ከፊቴ ቅድም… አምላኬ በውስጤ የሚመላለሠው ሃሳብ ተመክተህ መፍትሔም ትሠጠኝ ዘንድ እለምናለው። ለኔ ካሠብክ የኔን እንጀራ ማንም እንደማይበላው አውቃለው። የኔን ማዕድ ይህ ነው ካለከኝ ማዕድን እንዳገኝ እርዳታህን እሻለው። መፍትሔውን ካንተ እጠብቃለው… ካልሆነና ግን መረሻውን፣ መካሻውን በቶሎ ላክልኝ።”

Comments (1)
No comments yet